“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላነጋገሩን ወደ ሥራ አንገባም ብለናል” ወ/ሮ ነኢማ አሕመድ የፓርላማ አባል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች፣ሞቶችና ንብረት መውደምን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡን ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ማቅረባቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ለጥያቄዎችቻቸው ቀርበው ምላሽ ካልሰጧቸው ሥራቸውን መቀጠል እንደሚሳናቸው መናገራቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ያወጣው መግለጫ "ምንም አዲስ የሚያመጣው ነገር የለም" በሚል ትችት ቀርቦበታል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካላነጋገሩን ወደ ሥራ አንገባም ብለናል” ወ/ሮ ነኢማ አሕመድ የፓርላማ አባል