የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሐሙስ ተጠርቷል ተብሏል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ወር መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት

ሰሞኑን አከራካሪ በሆነው የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ማቋቋም ጉዳይና ወቅታዊ ሁኔታ እንዲወያይ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሐሙስ ተጠርቷል ተብሏል።

በኦሮምያ አካባቢ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በመዳከሙ፣ የካህናት እጥረት በመፈጠሩና ፤ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚቀድስና የሚያስተምር አገልጋይ በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት እንዲቋቋም ያቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጠው እንደሚፈልጉ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልኮ መመሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሰላም ቀሲስ ሰለሞን ቶልቻ በበኩላቸው፤ የተነሳው ችግር ተገቢ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን አቀራረቡና ችግሩን ለመፍታት በሚል የቀረበው አማራጭ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

አያይዘውም ጉዳዩ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱ ካለባት ችግሮች አንዱ መሆኑንን እና አገልግሎቱንም ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ነገር ግን “የብቻ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ማቋቋም”፤የሚለው ጥያቄው የቀረበበት መንገድ ቤተክርሲያኒቱን ወደፊት ሊያፈራርስ የሚችል አደገኛ አካሄድ ነው ብለውታል። ከዚህ አንፃር ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑም ሐሙስ ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ ለምልዓተ ጉባኤ ተጠርቷል ብለዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ለሐሙስ ተጠርቷል ተብሏል