የጃኖ ባንድ አባላት በሙዚቃ መግባባትና የመድረክ አያያዛቸው ከዚህ ቀደም ከነበሩት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ባንዶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በተመልካች ዘንድ የተለዩ እና ተወዳጅ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። በተለይም በወጣት ኢትዮጵያውያን ተመልካች ዘንድ። የሚጫውቷቸው አብዛኛዎቹ ሙዚቃዎች በቀድሞ ድምፃውያን የተዜሙ የሙዚቃ ስራዎች ናቸው። ሌላው ጃኖዎችን የተለዩ የሚያደርጋቸው ነባር የሙዚቃ ዜማዎችን በአሜሪካውያኑ የሮክ የሙዚቃ ስልት ደግመው በማቀናበር ለአድማጭ ማቅረባቸው ነው።
የጃኖ ባንድ ሲመሰረት ከቀድሞው የባንዱ ስራ አስኪያጀቶ ከነበሩት በአቶ አዲስ ገሰሰ አማካኝነት ሙያዊ አስተያየቶችን ስጥቶአቸዋል። አሜሪካዊው እውቅ ሙዚቀኛ Bill Laswell የጃኖ ባንድ አባላትን መቼ እንዳገኛቸው በአጭሩ ሲናገር፤
“ጃኖን የማውቃቸው ገና ሲሰባሰቡ ጀምሮ ነው። እናም እንዴት ቢሰሩ የተሻለ ስኬትን ሊያመጡ እንደሚችሉ የስራ ተሞክሮዬን አካፍያቸው ነበር። አሁን ባላቸው የሙዚቃ ችሎታና ጥንካሬ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከሮክ የሙዚቃ ስልት ጋር በማዛመድ የሰሩት ሙዚቃ በብዙዎች ተቀባይነቱን ስመለከት ደስታ ይሰማኛል።” ብሏል።
የጃኖ ባንድ አባላትና እውቁ አሜሪካዊው ሙዚቀኛ Bill Laswell ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ያደረጉትን አጭር ቆይታ ከበታች ያለውን ድምፅ በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5