በሳዑዲ አረቢያ በእሥር ላይ ሰለሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ በእሥር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በሳዑዲ አረብያ በችግር ውስጥ የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የፌደራል መንግሥት ፍቃደኛ ባለ መሆኑ ቀጥታ ከሳዑዲ ወደ መቀሌ ቢመጡ እንቀበላቸዋለን የሚል ደብዳቤ ለሳዑዲ ንጉሳዊ ቤተሰብ ላኩ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ደግሞ ሁለት ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ገልጿል።

በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 51/8 መሰረት የውጭ ግንኙነት ጉዳይ የፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን ያስረዱት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ፕሮፌሶር ካሳሁን ብርሃኑ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ተከተሉት የተባለው አካሄድ ሕገ መንግሥቱን የሚፃረር ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በሳዑዲ አረቢያ በእሥር ላይ ሰለሚገኙ ኢትዮጵያውያን