በአሜሪካ ለጥቁሮች የሲኒማ ጥበብ የውይይት መድረክ የከፈቱ ወጣቶች

መቅደስ ኃይሌ የሚዲያ ሽፋን ካገኙበት አንዱ የሂዩስተን ክሮኒክል ጋዜጣ ጋር፣ በጋዜጣው ምስል ላይ አብራት ያላችው ክሎይ ግሬይ ናት፡፡

ወጣት መቅደስ ኃይሌ በቴክሳስ የሂውስተን ከተማ ነዋሪ ናት፡፡ እንደ አብዛኛው ሰው ሁሉ እሷም እንዲሁ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በቤት ውስጥ ተገድበው ከቆዩ ወጣቶች መካከል ናት፡፡ ይህን አስጨናቂ ጊዜ አስደሳችና ውጤታማ ለማድረግ ክሎይ ግሬይ ከተባለች አፍሪካዊት አሜሪካዊት ጓደኛዋ ጋር በመሆን በድረ ገጽ ላይ የሚካሄድ MNC MOVIE CLUB የውይይት መድረክ ፈጥረዋል፡፡

ውይይቱ በአሜሪካ ውስጥ በጥቁር አሜሪካውያን እየተሰሩ የሚወጡ አዳዲስ ፊልሞችን በቡድን ሆኖ ማየትና መገምገም ነው፡፡ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎችም ይጋበዛሉ፡፡

ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተከታዮችን የፈጠረላቸው ከመሆኑም በላይ፣ በኦስካር ሽልማት አሸናፊ የሆኑ የፊልም ባለሙያዎችን ሳይቀር በውይይታቸው ላይ እንዲገኙ አድርጎላቸዋል፡፡

ለምሳሌ ቤሪ ጀንኪንስ በአሜሪካ እጅግ ተደናቂና ታዋቂ ከሆኑ የኦስካር ፊልም አሸናፊዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ሙን ላይትን ጨምሮ በርካታ ፊልሞችን መርቶ ጽፎ አዘጋጅቶ ለሽልማት ከበቁ ጥቂት ጥቁር አሜሪካውያን መካከል አንዱ ነው፡፡ ባንዳንዱም ዘርፍ አሸነፎ ሲሸለም የመጀመሪያው ነው፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር አንዱ ጥቅሙ ማስተሳሰር ነውና የነ መቅደስ መረብ ታዋቂ ሰዎችንም ወደ ነሱ የውውይት መድረክ መጎተት ጀምሯል፡፡

እንደ ሂውስተን ክሮኒክል ባሉ ጋዜጠኞችም ላይ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያስገኘላቸው መሆኑን መቅደስ ኃይሌ ተፈራ ትናገራለች፡፡ የዛሬው “የኢትዮጵያውያን በአሜሪካ” እንግዳ በማድረግ አነጋግረናታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በአሜሪካ ለጥቁሮች የሲኒማ ጥበብ የውይይት መድረክ የከፈቱ ወጣቶች