"የተፈታነው ከይቅርታም ሆነ ከምሕረት ጋር በተያያዘ አይደለም" ሁለቱ ጋዜጠኞች

የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድ

የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድ

የሽብር ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውና በጥፋተኝነት ውሳኔ እስር ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ጋዜጠኞች ዳርሴማ ሶሪና ካሊድ መሐመድን ጨምሮ ስድስት የሙስሊም ጉዳዮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በአመክሮ ከእስር መለቀቃቸውን ተናገሩ።

Your browser doesn’t support HTML5

"የተፈታነው ከይቅርታም ሆነ ከምሕረት ጋር በተያያዘ አይደለም" ሁለቱ ጋዜጠኞች

"የተፈታነው ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞችን መፍታትን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት የዛሬ ሣምንት በሰጠው መግለጫ መሰረት በይቅርታም ሆነ በምሕረት አይደለም ፍርዳችንን ጨረሰ በአመክሮ ነው” ብለዋል። አያይዘውም “መፈታት የነበረብን ከአንድ ወር በፊት በመሆኑ እንደውም እላፊ ታስረናል።” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

አሁንም የተፈታነው “በፍርድ ቤት የአመክሮ መብታችንን አስከብረን ነው” ብለዋል። ጋዜጠኛ ካሊድ እርሱና ሌሎች እስረኞች ከእስር እስከተፈቱበት ጊዜ ድረስ ድብደባን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምባቸው እንደነበር ገልጾ፤ “ይህንን ወደፊት በይፋ ለሕዝብ አሳውቃለሁ” ብሎናል።