የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ። የፍርድ ቤቱ ሂደት እስኪጠናቀቅ ከሀገር እንዳይወጡ የተሰጠው ትዕዛዝ ለፍርድ ቤት መድረሱ ሲረጋጥም እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰቷል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሥር ከታሰሩ ስምንተኛ ወራቸውን ያስቆጠሩትና ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት በማድረግ፣ የተለያዩ የሽብርተኛ ድርጅቶችን ሐሳብ የሚገልፁ ጹሑፎችን እንዲሁም ምስሎችን ይዛችሁ ተገኝታችኋል በሚል የወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙት የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በዋስ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ በተከሰሱበት ጉዳይም ዐቃቤ ሕግ አንድ ምስክር በዝግ አሰምቷል። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5