ኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ኤርትራ አቀኑ

  • ቪኦኤ ዜና
deputy minister health Ethiopia

deputy minister health Ethiopia

ኤርትራ ውስጥ የሕክምና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተነሡ ሰላሣ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ዛሬ መሸኘታቸውን የመንግሥቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

ኤርትራ ውስጥ የሕክምና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለመስጠትና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የተነሡ ሰላሣ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን የሕክምና ባለሙያዎች ዛሬ መሸኘታቸውን የመንግሥቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።

ባለሙያዎቹ ኤርትራ ውስጥ የሚቆዩት ለሁለት ወራት መሆኑ ተገልጿል።

የኤርትራ የበጎ ፍቃድ ዘማች ሐኪሞቹን ቡድን የሸኙት የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተመሣሣይ ተልዖኮዎች ወደ ሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች እንደሚደረጉ መናገራቸው ተዘግቧል።

ኤርትራ ዘማቹ የኢትዮጵያ የበጎ ፍቃድ ቡድን ያቀፈው 35 ጠቅላላ ሃኪሞችና አራት ስፔሻሊስቶችን መሆኑ ታውቋል።