ዲሞክራሲ ከየትም መጥቶ የሚጫን አይደለም ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ይሄን የሚያስከብረውን ለዜጎች ካለው ተቆርቋሪነት እና ኃላፊነት መሆኑን አስታውቋል።
አዲስ አበባ —
ለዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የቀረበውን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ረቂቅ ሕግ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የመንግሥት ኮሚኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ቃል- አቀባይ በኮንግረሱ የሚገኙ አንዳንድ ግለሠቦች የተለየ አቋም ሊይዙ ይችላሉ ብለዋል።
በዚህ ሳምንት መጀመርያ ለዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የአፍሪካ ንኡስ ኮሚቴ የቀረበው ረቂቅ ሕግ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ ያደረገ ነው።
የአፍሪካ ጉዳይ ንኡስ ኮሚተ ሊቀ-መንበር በሆኑት ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ የተጻፈውና HR- 2016 የተባለው ሕግ ያተኮረውም በወቅታዊው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ነው። የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚወስዷቸውን ያልተመጠኑ እርምጃዎች ያወግዛል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5