ሁለት የኢንዶኔዥያ ተዋጊ ጄቶች፣ "ያለ ፈቃድ" ወደ ኢንዶኔዥያ ያየር ክልል ገብቷል ያሉትን አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዛሬ ሰኞ በባታም ደሴት አይር ማረፊያ እንዲያርፍ ማስገደዳቸው ተገለጸ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት የኢንዶኔዥያ ተዋጊ ጄቶች፣ "ያለ ፈቃድ" ወደ ኢንዶኔዥያ ያየር ክልል ገብቷል ያሉትን አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዛሬ ሰኞ በባታም ደሴት አይር ማረፊያ እንዲያርፍ ማስገደዳቸው ተገለጸ።
የአየር ኃይሉ አፈ ቀላጤ እንዳስታወቁት፣ ቦይን ግ777 አውሮፕላን፣ ከባታም በስተደቡብ በሚገኘው የሀንግ ናዲም ዓለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በተሰኘው የሲንጋፖር ደሴት ላይ በሰላም እንዲያርፍ ተደርጓል።
የበረራ ቁጥሩ ETH 3728 ሆነውና ከአዲስ አበባ የተነሳው የኢትዮጵያው አውሮፕላን ወደ ሆንግ ኮንግ ነበር የሚያመራው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለሥልጣናት፣ ስለ ሁኔታው፣ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።