በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ሠራተኞች የቀድሞ ባልደረቦቻቸውን ለመዘከርና በቢሾፍቱው አደጋ ሕይወታቸው ለጠፋ ተሣፋሪዎች የፀሎትና የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በዋሺንግተን ዲሲና በአካባቢዋ የሚኖሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ሠራተኞች የቀድሞ ባልደረቦቻቸውን ለመዘከርና በቢሾፍቱው አደጋ ሕይወታቸው ለጠፋ ተሣፋሪዎች የፀሎትና የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅተዋል።
ሥነ-ሥርዓቱ በቨርጂንያው ኮሎምቢያ ፓይክ እና ሳውዝ ሃይላንድ መንገዶች ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ድርጅት ውስጥ ለፊታችን ዕሁድ፣ መጋቢት 8/2011ዓ.ም /MARCH 17/219/ በዋሺንግተን ሰዓት ከሰዓት በኋላ 2 PM እስከ 4 PM አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት እስኪሆን ይካሄዳል።
የዝግጅቱን አስተባባሪዎች አነጋግረናል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት።