የባሕል ቤት ለኢትዮጵያ - በክሊቭላንድ

ከክሊቭላንዱ የኢትዮጵያ የባሕል መስክ መሥራች አባላት ሁለቱ አቶ አክሊሉ ደምሴ እና Mr. Scott Embacher

ስለ ኢትዮጵያ ባሕል፣ ታሪክ እና ዘመን የጠገበ ሥልጣኔ የተሰየመ የባሕል መስክ ነው።

ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ሕዝቦች የባሕል መናሀሪያ የሆነችው የክሊቭላንድ ከተማ ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጎዳና እና ከአዋሳኙ የሮከፌለር መዝናኛ ፓርክ አቅራቢያ በተከለለው የልዩ ልዩ ውብ ባህላዊ ዕሴቶች መታሰቢያ ሥፍራ ዘንድሮ ለኢትዮጵያ የባሕል፣ ታሪክ እና ሥልጣኔ ቅርስ ሰላሳ ሶስተኛውን የባሕል መስክ ሰይማለች።

የኢትዮጵያ የባሕል ቤት በክሊቭላንድ

የዩናይትድ ስቴትሷ የኦሃዮ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ክሊቭላንድ “ሰላም እርስ በእርስ በመግባባት” በሚል ተልዕኮ ከ103 ዓመታት በፊት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1916 ዓም የተጀመረ ለየቅል የሆኑ ባሕሎችን አብሮነትና መልከ ብዙነት የሚያወድስ የከበረ ልማድ ባለቤት ናት።

የኢትዮጵያ የባሕል ቤት በክሊቭላንድ

በቅርቡ የተመሠረተውን ይህን የኢትዮጵያ የባሕል መስክ በአስተባባሪነት ካቋቋሙ ስድስት ኢትዮጵያውንና አሜሪካውያን አጋሮቻቸው ሁለቱን አወያይተናል።

Your browser doesn’t support HTML5

ከአቶ አክሊሉ ደምሴ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ከአቶ አክሊሉ ደምሴ ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከMr. Scott Embacher (በምርጫ ኢትዮጵያዊ ናቸው) ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከMr. Scott Embacher (በምርጫ ኢትዮጵያዊ ናቸው) ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ።