ተፈናቃዮች ወደ ጠለምት ወረዳ መመለሳቸውን ወታደራዊ እዙ አስታወቀ

የሰሜኑ ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ ከጠለምት አካባቢዎች ተፈናቅለው ነበር የተባሉ ከዐሥር ሺሕ በላይ ሰዎች፣ በአራት ዙሮች ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን፣ በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ እዝ አስታወቀ፡፡

የዕዙ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል መሰለ በለጠ፣ ለመንግሥታዊው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ፣ "ከትግራይ እና ከዐማራ ክልሎች ተወካዮች ጋራ በመተባበር ተፈናቃዮቹን የመመለስ ሥራ ተሠርቷል፤" ብለዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ተፈናቃዮች ወደ ጠለምት ወረዳ መመለሳቸውን ወታደራዊ እዙ አስታወቀ

የጠለምት ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ግን፣ "በተፈናቃይ ስም የህወሓት ታጣቂዎች ገብተዋል፤ ቀድሞ መግባባት ከተደረሰበት ውጭም፣ ቁጥሩ የበዛ ተፈናቃይ እንዲገባ ተደርጓል፤" ሲሉ ይከሳሉ፡፡

የሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ምክትል አስተዳዳሪ ከላሊ ሃጋዚ በተፈናቃዮች አመለላስ ሒደት እና በተሰነዘሩት ቅሬታዎች ላይ ምላሻቸውን ሊሰጡን ከተስማሙ በኋላ ስልካቸው ባለመነሣቱ ምላሻቸውን ለማካተት አልተቻለም፡፡