ትግራይ ክልል በትኬት ዋጋ መናር ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራሪያ ጠየቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የትግራይ ክልል ትራንስፖርትና መገናኛ ቢሮ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አክሱም ለሚከበረው ኅዳር ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል ተጓዦች ላይ "የተጋነነ" የትኬት ዋጋ ጭማሪ አድርጓል በማለት ወቀሳ አቅርቧል፡፡ በተጓዦች ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ፣ “አየር መንገዱ ለትግራይ ሕዝብ "ፍትሃዊ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል" እንደኾነና “ውሳኔው ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው” ቢሮው ገልጿል።

Your browser doesn’t support HTML5

ትግራይ ክልል በትኬት ዋጋ መናር ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ማብራሪያ ጠየቀ

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምጽ ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ታደለ መንግሥቱ፣ አየር መንገዱ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀናል ብለዋል፡፡ የአክሱም ከተማ የባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ዘረዳዊት ፀጋይ በበኩላቸው፣ የቲኬት ዋጋ ጭማሪው በጎብኝዎች ላይ ቅሬታ መፍጠሩን ገልጸው ተጓዦቹ ከአዲስ አበባ አክሱም ለደርሶ መልስ ጉዞ እስከ 42 ሺሕ ብር መክፈላቸውን ተናግረዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ኃላፊዎች አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ የጹሑፍ መግለጫ እንደሚያወጡ ገልጸውልናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።