በዝቋላ ተራራ ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት ዛሬም በአስተማማኝ ሁኔታ በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ ተነገረ።
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምሥራቅ 15 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ የሚገኘው ዝቋላ ተራራ በአቦዬ ገብረመንፈስ ቅዱስ ስም የቆመው ጥንታዊ ገዳም የሚገኝበት ሥፍራ ነው፡፡
በተራራው ላይ ያለው ገዳም መቃጠል የጀመረው መጋቢት ስምንት 2004 ዓ.ም መሆኑን አንድ እማኝ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ቃጠሎው ስፋት ያለውን የአካባቢውን ደን ማቃጠሉን እማኙ አመልክተው እሳቱ ወደገዳሙና በአካባቢውም ወዳለው ፀበል መቃረቡንም ጠቁመዋል፡፡
ስለቃጠሎው መንስዔ እኒሁ እማኝም ሆኑ ሌሎች የአካባቢው ሰዎች እንደማያውቁ ገልፀው ከተራራው ግርጌ ግን አክሳዮች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡