ከዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች /ብሎገሮች/ እና ጋዜጠኞች እሥር ቤት ቀርቶ የነበረው በፈቃዱ ኃይሉ በሃያ ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርጅ ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት አዝዟል።
አዲስ አበባ —
Your browser doesn’t support HTML5
ከዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች /ብሎገሮች/ እና ጋዜጠኞች እሥር ቤት ቀርቶ የነበረው በፈቃዱ ኃይሉ በሃያ ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርጅ ቤት አሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት አዝዟል።
ፍርድ ቤቱ በፈቃዱ ኃይሉ የወንጀል ክሡን እንዲከላከል ሲበይን ጉዳዩን በውጪ ሆኖ እንዲከታተል ዛሬ ወስኗል።
አቃቤ ሕግ “ተከሳሹ በዋስ ቢወጣ አሁንም ሕዝብን ለአመፅ የሚቀሰቅስ ፅሁፍ መፃፉ አይቀርምና መፈታቱን እቃወማለሁ” ቢልም ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ይህን ሊያደርግ ስለመቻሉ ምንም ማስረጃ አልቀረበም ብሏል።
የመከላከያ ምስክሮችንም እንዲያሰማ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ዝርዝሩን መለስካቸው አምኃ የላከውን ዘገባ ከያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡