የኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ተሰጥኦ ለማጎልበት እንደሚሠራ የአሜሪካ ኤምባሲ ገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ተሰጥኦ ለማጎልበት እንደሚሠራ የአሜሪካ ኤምባሲ ገለጸ

በኢትዮጵያ ለሥራ ፈጠራ እና የክህሎት መዳበር ጉዳዮች ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለጸው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በተለይ የአገሪቱ ወጣቶች እርስ በርስ ለሚማማሩባቸውና ለሚረዳዱባቸው መድረኮች ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡

በወጣቶች ላይ ለሚሠሩ ድርጅቶች መድረክ እንደሚያመቻች የገለጸው ኤምባሲው፣ በአገሪቱ የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች የሕይወት ተሞክሯቸውን እንዲያጋሩ እያደረገ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ኤምባሲው ከአዘጋጃቸው በርካታ መድረኮች ውስጥ፣ የሥነ ጥበብ ሞያተኞቹ ዓለማየሁ ታደሰ እና አርቲስት ሰላም ተስፋዬ የተገኙባቸው ይጠቀሳሉ፡፡ ሁለቱም አርቲስቶች፣ ለወጣቶች ይበጃሉ ያሏቸውን ምክሮች ለግሰዋል፤ ያለፉበትንም ውጣ ውረድ አጋርተዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።