የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ያገለገሉት ማርጋሪት ቻን ሥልጣን ሊለቁ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ማርጋሪት ቻን

የሥራ ዘመናቸውን አጠናቀው ሥልጣን የሚለቁት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ማርጋሪት ቻን፣ የዘንድሮውን የድርጅቱን ጉባዔ የከፈቱት አሁን አሁን ድርጅቱ፣ ዋጋውን እያጣ ነው የሚሉትን ሰዎች ትችት ጠንከር ባላ ኃይለ ቃል በማስተባበል ነው፡፡

የሥራ ዘመናቸውን አጠናቀው ሥልጣን የሚለቁት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ማርጋሪት ቻን፣ የዘንድሮውን የድርጅቱን ጉባዔ የከፈቱት አሁን አሁን ድርጅቱ፣ ዋጋውን እያጣ ነው የሚሉትን ሰዎች ትችት ጠንከር ባላ ኃይለ ቃል በማስተባበል ነው፡፡

ማርግሪት ቻን ለአለፉት አሥር ዓመታት የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ካገለገሉ በኋላ ሥልጣን ሊለቁ ሲሆን ነገ ማክሰኞ ለሚመረጥ ይህን ለዓለም ጤና ጥበቃ ዋና ቁልፍ የሆኑ ድርጅት ለሚመራ ሰው ሥልጣኑን ሊያስረክቡ ነው፡፡

ዛሬ ጄኔቫ ውስጥ ለተሰበሰበ የዓለም ጤና ድርጅት ጉባዔ የመጨረሻ ንግግራቸውን ሲያደርጉ ቻን የሥራ ዘመናቸውን ሥኬታማ ውጤት የዘረዘረ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ባለፉት አሥር ዓመታት የአስተዳደር ዘመናቸው በሕዝባዊ ጤና ጥበቃ ሰለተደረገው ግስጋሴ በዚህ ወር ይፋ ያደረጉትን ሪፖርት ነው ጨምቀው ያቀረቡት፡፡

ሊሻስ ላይን ከጄኔቭ ዘግባለች፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የዓለም ጤና ድርጅትን በዳይሬክተርነት ያገለገሉት ማርጋሪት ቻን ሥልጣን ሊለቁ ነው