ዩኒቨርሲቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ፣ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም

የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)

ዩኒቨርሰሲቲዎች ውጤታማ ሥራ ካላከናወኑ፣ ህልውናቸው ላይቀጥል እንደሚችል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ አስጠነቀቁ፡፡ በሀገሪቱ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋራ ዛሬ የአፈፃፀም ኮትራት የፈረሙ ሲሆን፣ ሥራዎቻቸውም፣ በዚሁ ኮንትራት መሰረት እንደሚለካ ተገልፆዋል፡፡ ወደፊት ለዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው በጀት፣ የሥራ አፈፃፀማቸውን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን የገለፁት ሚኒስትሩ፣ ከዛም አልፎ ዩኒቨርሲቲዎቹ፣ ውጤታማ ካልሆኑ ወደ ቴክኒክ ማሰልጠኛነት የሚቀየሩበት ኹኔታ ይኖራል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በበኩላቸው፣ እርምጃው ውጤትን ለመመዘን ስለሚያስችል ተቋማቱን ያነቃቃቸዋል በማለት ገልፀዋል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ዩኒቨርሲቲዎች ውጤታማ ካልሆኑ፣ ህልውናቸው ሊቀጥል አይችልም