ህወሓት ይዟቸው የነበሩ በርካታ ቦታዎች መለቀቃቸውን መንግሥት አስታወቀ

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

ህወሓት ይዟቸው የነበሩ በርካታ ቦታዎች መለቀቃቸውን መንግሥት አስታወቀ

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትና ልዩ ልዩ የፀጥታ ኃይሎች መንግሥት በአሸባሪነት በፈረጀው ህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር የነበሩ ብዙ ቦታዎች በጥቂት ቀናት ማስለቀቃቸውን የመንግሥት አገልግሎት ሚኒስትሩ ይፋ አደረጉ።

ሚኒስትሩ የማጥቃቱ እርምጃ መቀጠሉንም ተናግረዋል። ህወሓት በበኩሉ “መንግሥት በሲቪል ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ ጉዳት አድርሷል” ሲል ከሷል።