በትግራይ ክልል ባጋጠመው የመኪና አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ

  • ግርማይ ገብሩ
የትግራይ ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ካህሳይ

የትግራይ ክልል የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ካህሳይ

ትናንት ውቅሮ ከተማ ውስጥ በደረሰ የመኪና አደጋ አምስት የክልሉ የሴቶች ቢሮ ሰራተኞች ህይወታቸው ኣልፉዋል።

ከሟቾቹ መካከል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የክልሉ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሙሉ ካህሳይ እና ሌሎች ሶስት ከፍተኛ ባለሙያዎች እንዲሁም የመኪናው አሽከርካሪ ጭምር መሆናቸውን ታውቋል።

አደጋው የደረሰው በስራ ምክንያት ከውቅሮ ወደመቀሌ ሲመለሱ እንደነበር ተጠቅሷል።

በትግራይ ክልል የተሽከርካሪዎች አደጋ ካለፈው ዓመት ስድስት በመቶ መጨመሩን የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ ገልጿል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ባጋጠመው የመኪና አደጋ አምስት ሰዎች ሞቱ