በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ታስረው የነበሩ መምህራን መፈታታቸውን ተናገሩ 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእስር ላይ የነበሩና 66 ይኾናሉ የተባሉ መምህራን መፈታታቸውን የዞኑ መምህራን ማኅበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቀ።

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ከእስር የተለቀቁ መምህራን፣ በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸንና ሕክምና ተከልክለው እንደነበር ገለጹ።

በኮሬ ዞን የሳርማሌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፣ ታሰሩ የተባሉ መምህራን ቁጥር በጣም አነስተኛ እንደነበር ገልጸው፣ "ሁሉም ከእስር ተለቀዋል" ብለዋል። ድብደባ ተፈጸመ የተባለውም ከ"እውነት የራቀ ነው" ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።