ቅሬታቸውን የሚፈታ ማጣታቸውን ነጋዴዎች ገለጹ

መሸጫ ሱቆቻቸውን የዘጉ ነጋዴዎች

መንግሥት የተመነባቸውን የቀን ገቢ ግምት ተቃውመው ቅሬታ ያቀረቡ ነጋዴዎች ቅሬታቸው እየታየ እንደሚገኝ ቢያስታውቅም ነጋዴዎች ግን ቅሬታቸውን የሚፈታ አካል እንዳጡ ይናገራሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

ቅሬታቸውን የሚፈታ ማጣታቸውን ነጋዴዎች ገለጹ

አዲሱ የቀን ገቢ ግምት ተግባራዊ የተደረገባቸው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እስካሁን የተፈታላቸው ቅሬታ እንደሌለ ገለጹ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሻምቡ ከተማ ነዋሪ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ነጋዴዎች ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ገልፀው ነገር ግን በስብሰባ ላይ የተናገሩ ሰዎች ታስረዋል ሱቆችም በከፊል ተዘገተዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እስካሁን 80 በመቶ የሚሆኑ ቅሬታዎች በአግባቡ እየተፈቱ ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ክልልም በበኩሉ ከነጋዴው ማኅበረሰብ ጋር በአግባቡ መወያየቱን እና ቅሬታዎች እየተፈቱ መሆናቸውን አስታውቋል። ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት