የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምሬት

የምንሰማው ሳይሆን የሚሰማን ነው የምንፈልገው"- ነጋዴዎች

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምሬት

ባለፈው ሳምንት ቀዳሚ ርእስ ሆኖ የሰነበተው በአዲስ አበባ ከተማ ነጋዴዎች ላይ የተደረገው አዲሱ አማካኝ የቀን ገቢ ትመና አሁንም ነጋዴዎችንና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን አላግባባም። ገቢዎች የገቢ ግምት ትመናው የቀን ገቢን እንጂ ተከፋይ ግብርን አያሳይም ሲል የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት በበኩላቸው ግምቱ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን ከፍተኛ የገቢ ግብር ማሳያ በመኾኑ ሊቀበሉት እንደማይችሉ ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ የታክስ ፕሮግራም እና ልማት ሥራዎች ዘፍር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ነጻነት አበራ በበኩላቸው የቀን ገቢ ግምቱ የተሠራው በጥናት ላይ ተመሥርቶ እንደሆነ ገልፀው ሁኔታውን ለመረዳትም መደማመጥ እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምሬት