በምዕራብ ጎንደር ዞን ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ሱዳናውያን ስደተኞችን፣ ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር እየሠራ መኾኑን፣ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
በተቋሙ፥ የኩመር፣ የአውላላ እና የዓለምዋጭ መጠለያ ጣቢያዎች አስተባባሪ አቶ ታምራት ደምሴ፣ የሱዳን ስደተኞችን “አፍጥጥ” ወደሚባል ቦታ ለማዛወር እንቅስቃሴ መጀመሩን ለቪኦኤ ገልጸዋል፡፡
ከመጠለያ ጣቢያቸው ለቀው መንደር ዳር መኖር ከጀመሩ አንድ ወር እንደሞላቸው የሚናገሩት የሱዳን ስደተኞ ደግሞ፣ ደግሞ፣ የአካባቢው የጸጥታ ችግር እና የአገልግሎት እጥረት እንደሚያሳስባቸው ገልጸው፣ ፍላጎታቸው ከኢትዮጵያ ውጪ ወደ ሦስተኛ ሀገር መሔድ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡