መንግሥት የኑሮ ውድነትን የማሻሻል እርምጃ አካል በማድረግ 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ አያስገባ መሆኑን አስታውቋል
አስተያየታቸውን የሰጡን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ መንግሥት እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ በዘይት ላይ የተወሰነ የዋጋ መሻሻል መኖሩን ገልጸው፣ ኾኖም የዋጋ ንረቱ ፈታኝ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
የምጣኔ ኃብት ተንታኝ የኾኑት አቶ አማንይሁን ረዳ፣ በሀገር ውስጥ በበቂ መጠን ማምረት እስኪቻል ድረስ፣ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግሥት ከውጭ የሚገቡ የፍጆታ ምርቶችን በብዛት ማስመጣቱን መቀጠል ይጠበቅበታል ይላሉ፡፡