አነጋጋሪው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀ ማግሥት በሕዝቡ ዘንድ ከተፈጠረው ስሜት የሚነሳው ውይይት፤ ከአዋጁ ባሻገር የአገሪቱን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ይዞታ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ይመረምራል።
የአዋጁን ሕጋዊ መሰረት፣ የዜጎችን መብት ጥበቃና ይልቁንም ደግሞ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩትን ግጭቶች እና የሚያስከትሉትን አደጋ የመከላከል ግዴታ እና አስፈላጊነት በትይዩው ይመለከታል።
ተወያዮች:- ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ፤ እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የOld Dominion University የPublic Management and Public Policy መምሕር እና የግጭት አፈታት ባለ ሞያ፤
አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ፤ የሕግ ባለ ሞያ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕገ መንግሥት እና የመገናኛ ብዙሃን ህግ መምህር እንዲሁም፤
በዩናይትድ ስቴትሷ የዋሽንግተን ሲያትል ከተማ በተካሄደው አገራዊ ጉባኤ ለመሳተፍ ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡት የሰማያዊ ፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ናቸው። የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5