ለወራት እስር ከቆዩት ጋዜጠኞች አንዱ ተለቀቀ

አናንያ ሶሪ

“ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ኦነግና ግንቦት ሰባት ከሚባሉት ድርጅቶች ግንኙነት ፈጥራችሁ ተንቀሳቅሳችኃል የሚል ነው። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድ የሚባል ኮሚቴ ጎብኝቶን ነበር በአንድ ወቅት። የነበሩትን ችግሮች፤ አዋጁ ግለሰቦችን በቂም በቀል ለማጥቂያነትና አስፈጻሚዎች የአዋጁን መንፈስ ባለመረዳት ጉቦ ለመብያነት ጭምር እንዳዋሉት፤ በተለያዩ አስቂኝ ምክኒያቶች ሳይቀር የገቡ መኖራቸውን ገለጥናላቸው።” አናንያ ሶሪ።

Your browser doesn’t support HTML5

ለወራት እስር ከቆዩት ጋዜጠኞች አንዱ ተለቀቀ


የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ለወራት እስር ላይ የቆየው ጋዜጠኛና የኢንተርኔት አምደኛ አናንያ ሶሪ ዛሬ ተለቀቀ።

በተመሳሳይ አብረውት የታሰሩት ጋዜጠኛና የኢንተርኔት አምደኛ ኤልያስ ገብሩና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባል ዳንኤል ሽብሩ እስካሁን ያለመለቀቃቸው ታውቋል።