በተለይ ከአማራ ክልል ሄደው በደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው በአካባቢው ባለሥልጣናት ሕገወጥ በመባላቸው የመሬት ይዞታዎቻቸውን እያስረከቡ ወደአዲስ አበባ መሰደዳቸውን ቀጥለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡን ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ቢሮ ደጋግመን ላደረግነው ጥሪ መልስ አላገኘንም፡፡ ጥረታችንን እንቀጥላለን፡፡
ያለፈውን ሌሊት በመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ ቅጥር ግቢና ፅ/ቤት ተፋፍገው ካሣለፉት 110 ተፈናቃዮች ጋር ቆይታ ያደረገው እስክንድር ፍሬው ያጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡