ኢትዮጵያ ፍላጎቷን ለማሟላት ቢያንስ አስር ወደቦች ያስፈልጋታል – የጅቡቲ ሚኒስትር

ጅቡቲ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ፍላጎቷን ለማሟላት ቢያንስ አስር ወደቦች ያስፈልጋታል – የጅቡቲ ሚኒስትር

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት፣ ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ድንበር በ100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ታጁራ ወደብ ኢትዮጵያ እንድትጠቀምበት ማቅረቧን የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሉ ዩሱፍ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ሆኖም ይህ አማራጭ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ለመገንባት ያላትን ፍላጎት እንደማያካትት ሚንስትሩ አመልክተዋል።