የማኅበራዊ መገናኛዎች መዘጋት የበይነ መረብ ግብይት አስተጓጎለ

Your browser doesn’t support HTML5

የማኅበራዊ መገናኛዎች መዘጋት የበይነ መረብ ግብይት አስተጓጎለ

በኢትዮጵያ አንዳንድ የማኅበራዊ ሚድያ መገናኛዎች መዘጋታቸው የበይነ መረብ ግብይቱን እንደጎዳው አንድ የዘርፉ ባለሙያ ገለፁ፡፡

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ኢትዮጵያ የተባለው ማሕበር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ባህሩ ዘይኑ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ የማኅበራዊ ሚድያ መገናኛዎቹ መዘጋት፣ ቀደም ሲል በመነቃቃት ላይ የነበረው የበይነ መረብ ግብይት እንዲቀዛቀዝ ያደረገ ሲሆን፤ ሁኔታው በኢኮኖሚው ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ አለው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን መዝጋት የህብረተሰቡን መረጃ የማግኘት መብት እና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚጋፋ ተግባር ስለሆነ ገደቡ መነሳት አለበት ብሏል።

የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።