ሰባት የበግ ነጋዴዎች በፋኖ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ገለጹ

በኦሮምያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ፣ ከአገምሳ ከተማ ወደ ጎጃም ጫቡ ገበያ ለንግድ በመኪና በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ የፋኖ ታጣቂዎች ፈጸሙት በተባለ ጥቃት፣ ሰባት የበግ ነጋዴዎች መገደላቸውን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሟች ቤተሰቦች ገለጹ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሰባት የበግ ነጋዴዎች በፋኖ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ገለጹ

ለጥቃቱ ተጠያቂ ነው ከተባለው የፋኖ ታጣቂ ቡድን በዚህ ጉዳይ ላይ በቀጥታ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም። ኾኖም በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኙት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ‘የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት’ መሪ እንደሆኑ የነገሩን አቶ እስክንድር ነጋ፣ ከአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ጋራ በቅርቡ ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ቡድኑ እንዲህ ያለውን አድራጎት በጽኑ እንደሚያወግዝ ተናግረዋል። "መንግሥትን የምንፋለመውም በእንዲህ ያሉ አድራጎቶች ምክንያት ነው" ማለታቸው ይታወሳል። ከመንግሥት ባለሥልጣናትም ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።