የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዛሬ መጀመሩን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ  

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዛሬ መጀመሩን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ  

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል አስጀምረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአክሲዮን ሽያጭ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ በቀጣይነት ኢትዮቴሌኮምን ጨምሮ የሌሎች ኩባንያዎች የድርሻ ሽያጭ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ለህዝብ የሚሸጠው በድምሩ ወደ 30 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለውን 100 ሚሊዮን አክሲዮን እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የአንድ አክሲዮን ዋጋ 300 ብር ሲሆን፣ መግዛት የሚቻለው ከ33 እስከ 3 ሺህ 333 እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡