ለአንድ ትሪሊዮን የተቃረበው የ2017 በጀት እና የባለሞያዎች ምልከታ

ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ለመጪው የኢትዮጵያ 2017 በጀት ዓመት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ971ነጥብ2 ቢሊዮን ብር(17 ቢሊዮን ዶላር) ዓመታዊ በጀት ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፣ የበጀት ረቂቁ በቀረበበት ወቅት ለምክር ቤቱ እንዳስረዱት፣ ካለፈው ዓመት 21 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ለአንድ ትሪሊዮን የተቃረበው የ2017 በጀት እና የባለሞያዎች ምልከታ

በጉዳዩ ላይ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች፣ የበጀት ጉድለቱ ከፍተኛ መኾኑንና ከበጀቱ ብዙ ድርሻ ለዕዳ ክፍያ እንደሚውል በመጥቀስ፣ በበጀቱ ውጤታማነት ላይ ጥያቄ አንሥተዋል።

አስተያየት እንዲሰጡን የጋበዝናቸው ሦስት የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች፣ ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ፣ ዶክተር አረጋ ሹመቴ እና አቶ ፋሲል ጣሰው ናቸው።