በሊባኖስ የአየር በረራዎች መቋረጥ ዜጎችን በማስወጣት ሂደት ላይ እክል መፍጠሩን ኢትዮጵያ አስታወቀች

  • ቪኦኤ ዜና

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

Your browser doesn’t support HTML5

በሊባኖስ የአየር በረራዎች መቋረጥ ዜጎችን በማስወጣት ሂደት ላይ እክል መፍጠሩን ኢትዮጵያ አስታወቀች

ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከ5ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን ቢመዘገቡም፣ የአየር በረራዎች በመቋረጣቸው ዜጎችን በማስወጣት ሂደት ላይ እክል መፍጠሩን ኢትዮጵያ አስታወቀች።

ኾኖም እስካኹን በሊባኖስ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 125 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ በመንግሥት በኩል ሕጋዊ ሰነድ ያሌላቸውን ጨምሮ ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት ጥረቱ ቀጥሏል ሲሉም ተናግረዋል፡፡