በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ተካሔደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኀይሉ

በኢትዮጵያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጨምሮ በአራት ክልሎች፣ ትላንት እሑድ፣ የስድስተኛው ዙር ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ መካሔዱን፣ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኀይሉ፣ የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክተው፣ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ምርጫው፥ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች መከናወኑን ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ ተካሔደ

በጸጥታ ችግር ምክንያት ምርጫ ያልተካሔደባቸው 40 የምርጫ ጣቢያዎችም እንዳሉ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

ምርጫው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ሲካሔድ፣ ከ10 ዓመታት በኋላ እንደኾነ ያመለከተው የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን መሪ ለመምረጥ ዕድል መስጠቱን ጠቅሶ፣ ሒደቱም በሰላም መጠናቀቁን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡