የ “ጫካው” ስደተኞች አካባቢውን ለቀው ወተዋል

  • ቆንጂት ታየ

ካሌ ከምትባለው የፈረንሳይ ሰሜናዊ ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘው ስደተኛ ሰፈር ለቀው ሲወጡ

ካሌ ከምትባለው የፈረንሳይ ሰሜናዊ ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘውና “The Jungle” ወይም “ጫካው” ተብሎ በሚታወቀው መጠለያ ካምፕ እጅግ በከበደ ጉስቁልና የሚኖሩት ስደተኞች ያላቸውን የግል ዕቃቸውን ይዘው በተዘጋጁ ኦቶቡሶች ተወስደዋል።

የፈረንሳዩ መንግስት ስደተኛው ወደሌሎች የሀገሪቱ ኣካባቢዎች ከተዛወረ በኋላ የጥገኝነት ማመልከቻ ለማስገባት እንደሚፈቀድ ተናግረዋል የሀገር ግዛት ሚኒስትሩ በርናንድ ካሳኖቭ “ሰብዓዊ ግዴታ” ሲሉ በጠሩት የካሌውን ሰፊ የስደተኛ ካምፕ የመዝጋት ርምጃ በተረጋጋ ሁኔታ ተከናውኗል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የስደተኞቹ ጉዳይ እና የካምፑ መዘጋት በፈረንሳይና እንግሊዝ እዚያው ፈረንሳይ በከተሞቹነዋሪዎች ኣንዲሁም በግብረ ሰናይ ድርጅቶች ዘንድ ስፋት ያለው ውዝግብ የቀሰቀሰ ነው።

ወደ 8 ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች በአስከፊ ሁኔታ እንደሚኖሩበት በሚነገረው በዚህ የስደተኛ ሰፈር ከኢትዮጵያ፣ከኤርትራ እና ከአፍጋኒስታን የተሰደዱ ስደተኞች ይገኙበታል።

ከኢትዮጵያ የሚሆኑትን በአስከፊ ሁኔታ የሚኖሩትን ስደተኞች ወደ ሌሎች የስደተኞች ሰፈሮች የማዛወሩ ሂደትአንድ ሳምንት ያህል ሊወስድ ይችላል።

ፍልሰተኞቹ በፈረንሳይ ዙርያ በሚገኙ የስደተኞች ሰፈሮች እንዲሰፍሩ ይደረጋል። ጥገኝነት የመጠየቅ እድልም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ይሁንና አንዳንዶቹ ስደተኞች በእንግሊሽ ቻነል በኩል ወደ ብሪታንያ መዝለቅ ስለሚፋልጉ ወደተባሉት ሰፈሮች አንሄድም ሊሉ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።

ቆንጅት ታዬ ዘገባ አላት

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የ “ጫካው” ስደተኞች አካባቢውን ለቀው ወተዋል