እስረኞቹ በምርመራ ወቅት አሰቃቂ ተግባር እንደተፈፀመባቸና ይህንንም ችሎት በሚቀርቡበት ወቅት እንደሚናገሩ አንዳንዶቹም ልብሳቸውን ገልጠው የተጎዳውን የሰውነታቸውን ክፍል ለችሎት እንደሚያሳዩ ጠበቀቻቸው ተናግረዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በአስተሳሰብና በአመለካከት ልዩነታቸው ብቻ በአሸባሪነት ተፈርጀው በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞችን ለማሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአንድ ቀን ዘመቻ ማድረጋቸውን አስተባባሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የእስረኖቹ ቁጥር ለጊዜው እንደማይታወቅ የገለጹት አስተባባሪዎቹ በኦሮሚያና በአማራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተሳትፋችኋል በሚል በሽብር የተከሰሱት ሰዎችች ቁጥር ከ1,500 እንደሚበልጥ ይናገራሉ።
በአሁኑ ሰዓት 900 ለሚደርሱ እስረኞች ጥብቅና ከሚቆሙ ጠበቆች መካከል የተወሰኑት ፤ ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ “እስረኞቹ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ጊዜ ብልታቸው ላይ የውኃ ላስቲክ እየተንጠለጠለ እንደሚሰቃዩ ከመግለፅ ጀምሮ አሰቃቂ ድብደባ እንደሚፈፀመባቸው ለፍርድ ቤት ያስረዳሉ” ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5