Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ በአብዛኛው በአገር ውስጥ ምርት ላይ ጥገኛ በመሆኗ እና በሌሎች ምክንያቶች የምግብ ዋጋ አስቀድሞ የተፈራውን ያህል ያለመጨመሩን የጠቀሰው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመለከተ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ትላንት የጠቀሰው ሪፖርት፣ ከውጭ በሚገቡ የፍጆታ እቃዎች ላይ ግን ከፍ ያለ ጭማሪ መታየቱን አመልክቷል፡፡
እስካሁን የምግብ ዋጋ ጭማሪዎች ቢኖሩትም የተጠበቀውን ያህል ጭማሪ ሳይታይበት ለመቀጠሉ የተለያዩ ምክንያቶችን የሚያስቀምጡት የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎችበበኩላቸው፣ በቀጣይነት ግን ከመደበኛው በተለየ ከፍ ያለ ጭማሪ የሚያስከትሉ ሁኔታዎችና እርምጃዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡