ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለፈው ሰሞን ከቅዳሜ የካቲት 23/2013 ጀምሮ መንግሥት ለሁለተኛ ጊዜ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረጉን ገልጿል፡፡ ይህም እየተባባሰ ነው በተባለው የሸቀጦች ዋጋ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሰጡት መግለጫ “ለኑሮ ውድነቱ ዋነኛ ከሆኑት ጉዳዮች መካከል የነጋዴዎች አሻጥር መሆኑን ደርሰንበታል” በማለት በአዲስ አበባ ክ30ሺ በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ እምርጃ መውሰዱን አስታውቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚ ክፍለ ትምህርት መምህራን የሆኑት ዶ/ር አጥናፉ ገ/መስቀልና ዶ/ር ዘርአየሁ ስሜ ግን ለኑሮ ውድነትና ዋጋ ግሽበት ዋነኛ ምክንያቱ የፋይናስ አስተዳደር ድክመት እና ከምርጫ 97 በኋላ እየተባባሰ የመጣው የኢኮኖሚ ለውጥ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያይዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5