Your browser doesn’t support HTML5
በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋባዥነት በቅርቡ ከተካሄደው የዋሽንግተኑን የአፍሪካ ፕሬዝዳንቶች ጉባኤ ትይዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትና ተጋባዥ እንግዶች የተሳተፉባቸው ስብሰባዎች ተካሂደዋል።
በእነኚህ ስብሰባዎችም በዋናው የፕሬዝዳንቶቹ ጉባኤ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባ ነበር ያሏቸውን አሳሳቢ የማኅበረሰብ ልማትና ብልጽግና፥ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ የተመለከቱ በርካታ ርእሰ ጉዳዮች አንስተዋል።
ከስብሰባዎቹ ተሳታፊዎች አንዷ የሆኑት የቀድሞዋ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ሊቀመንበር ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በውይይቶቹ የተነሱትን ጭብጦች መነሻ በማድረግ ባቀረቡት ጽሁፍ ይዘት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል።