ኢትዮጵያ አልሻባብን መዋጋቷን እንደምትቀጥል አስታወቀች

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ አልሻባብን መዋጋቷን እንደምትቀጥል አስታወቀች

ጦሯ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጣ ቢጠበቅም፣ ኢትዮጵያ አልሻባብን መዋጋቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ “በየትኛውም ሁኔታ አልሻባብን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት፣ ራሷን ነጻ አገር አድርጋ ከምትቆጥረው ከሶማሊላንድ ጋራ በተፈረመው የመግባቢያ ሰምምነት ሳቢያ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ውጥረት ተባብሶ በቀጠለበት ወቅት ነው፡፡

በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ኢትዮጵያ እንደማትሳተፍ የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ቅዳሜ ዕለት መናገራቸው ይታወቃል፡፡