በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው መዝግብ ከተከሰሱት ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት ተከራከሩ 

የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ

በአማራ ክልል በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መሀል ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ፣ በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው መዝግብ የሽብር ክስ ከተመሰረተባቸው 52 ተከሳሾች መካከል 16ቱ ዛሬ በፍርድ ቤት ቀርበው፣ ወንጀሉን አለመፈፀማቸውን በመግለፅ ተከራክረዋል። ተከሳሾቹ የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡት፣ "የአማራን ክልል መንግሥት በኃይል ከሥልጣን ለማውረድ" ሞክራችኃል በማለት የቀረበባቸውን ክስ ተቃውመው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ተከትሎ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ የተሻሻለውን ክስ ለፍርድ ቤት ከአቀረበ በኋላ ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው መዝግብ ከተከሰሱት ውስጥ የተወሰኑት በፍርድ ቤት ተከራከሩ 

በአማራ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጋራ በተያያዘ ተከሳሾቹ በቁጥጥር ስር ውለው አዋሽ አርባ እና ሰመራ በሚገኘው የእስረኛ ማቆያ ለወራት በቆዩበት ወቅት ደርሶብናል ያሉትን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲመረምር በፍርድ ቤቱ ታዞ የነበረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንም የምርመራውን ውጤት ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በፈፀሙ አካላት ላይ ምርመራ እንዲደረግ እና ተጠያቂነት እንዲኖር ምክረ ሐሳብ ማቅረቡን የተከሳሾች ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።