Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዐዲስ ሥራ አስፈጻሚ መረጠ። አምስት ፓርቲዎች ምርጫውን እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው ጠቅላላ ጉባዔ፣ ዐዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መምረጡን እና የም/ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ ማፅደቁን ዋና ጸሐፊው አቶ ደስታ ዲንቃ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም፣ የሥራ አስፈጻሚው ሥልጣን በማብቃቱ ምርጫ ቦርድ ጉባዔ እንዲጠራ የጠየቁ ስድስት ፓርቲዎች በበኩላቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በተካሔደው ጉባዔ የተላለፉ ውሳኔዎችን አንቀበልም ማለታቸውን የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ቢሉይ አብርሃም ኃይማኖት ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።