የትግራይ ክልል እርዳታ ለጋሾች ቅሬታ እና የመንግሥት ምላሽ

  • እስክንድር ፍሬው

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም

መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ለማድረስ ማነቆ ናቸው የተባሉ አሠራሮችን ማስተካከሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ረዳት ቃል አቀባይ ትናንት ሲናገሩ ወደ ትግራይ እርዳታ ለማድረስ ብቸኛ የሆነው የአፋር መስመር ተደራሽ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

"አሁን በአካባቢው እንቅፋት እየፈጠረ ያለው የህወሓት ጠብ አጫሪነት ነው" ያሉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሃላፊ ግን "የተደራሽነት ችግር ጥያቄ መቅረብ ያለበትም ለዚሁ ቡድን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ክልል እርዳታ ለጋሾች ቅሬታ እና የመንግሥት ምላሽ