ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ዛሬ በፈርንሳይ ጉዞ ጀምረዋል። ከነገ በስቲያም ፍራንክፈርት ውስጥ ከ20 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ዜጎችን ያገኛሉ ተብሏል። ስለ ዝግጅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም፣ በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር መርጋ በቃና እና በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ኃይለሚካኤል አበራን አነጋግረናቸዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከነገ በስቲያ ረቡዕ በጀርመን ውስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ጋር ፍራክፈርት ከተማ ላይ ለሚኖራቸው ፕሮግራም በብዙ የአውሮፓ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ወደዚያው እየሄዱ መሆኑንና ብዙዎችም ለመሄድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አምባሳደሮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮ ባደረጉላቸዉ ግብዣ ዛሬ ፓሪስ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ነገ ደግሞ የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከልን አግኝተው ለውይይት ይቀመጣሉ ተብሏል።
አሥራ አንድ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች በሚሳተፉበት በአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ በሚያተኩር ስብሰባ ላይም ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5