Your browser doesn’t support HTML5
የፖስፖርት የግዜ ገደብ ወደ 10 ዓመት ሊራዘም ነው
በኢትዮጵያ የሚሰጠው ፖስፖርት፣ የአገልግሎት ቆይታው ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል፣ የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ከአንድ ወር በኋላ በሚጀመረው አዲስ አሠራር መሰረት የሚሰጠው ፖስፖርት ለ 10 ዓመት የሚያገለግል ይሆናል ብለዋል፡፡
መሥሪያ ቤቱ፣ በዚህ ዓመት የቤት ለቤት የፓስፖርት ማደል አገልግሎት እንደሚጀምርም ዋና ዲሬክተሯ ተናግረዋል፡፡