ከታጠቁ ኃይሎች ጋራ ንግግር እየተደረገ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ተናገሩ 

Your browser doesn’t support HTML5

ከታጠቁ ኃይሎች ጋራ ንግግር እየተደረገ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድጋሚ ተናገሩ 

በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል መግባባት ለመፍጠር የአፍሪካ ኅብረትን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ጥረት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ አሕመድ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች የሰላም ጥረቶች እስካሁን እንዳልተሳኩ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተደራሽነት ጥረቷን በሰላማዊ መንገድ እንደምትቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መንግሥታት መካከል ያለውን አለመግባባት የሚያንፀባርቅ ንግግርም አድርገዋል፡፡