Your browser doesn’t support HTML5
ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ የቆዩ ከመቶ በላይ የሠራዊቱ አባላት የነበሩ የትግራይ ተወላጆ ወታደሮች እና መኮንኖች አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ወታደሮቹና መኮንኖቹ በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እስከ ሞት ቅጣት የሚደርሱ ውሳኔዎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የቆዩ መሆናቸውንም የመከላከያ ሚንስቴር አመልክቷል።
ይቅርታ ቦርዱን ውሳኔ በመቀጠል እንዲለቀቁ የተወሰነው፣ መንግሥት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረውን ጦርነት ለማቆም በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ሥምምነት ይበልጥ ለማፅናት ቁርጠኛ በመሆኑ ነው ሲል የመከላከያ ሚኒስቴር አክሏል።