ነባሩን የብራና ዝግጅት እና የብራና ላይ ሥራዎች ለዐዲሱ ትውልድ የማስተዋወቅ፣ ቅርሱንም የማስቀጠል ዓላማ ያለው ዐውደ ርእይ፣ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።
“ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ” በሚል ርእስ በተካሔደው ዐውደ ርእይ ላይ፣ የብራና መጻሕፍት እና ሥዕላት እንዲሁም ሌሎች የሥነ ጽሑፍ እና የሥነ ጥበብ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል፡፡
የዐውደ ርእዩን አዘጋጆች እና ጎብኚዎች አስተያየት በማካተት፣ ኬኔዲ አባተ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡